ስደተኛው ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ


ከሁሉም አስቀድሞ፤ ስደተኛ ማለት ምንድን ነው? ማነውስ ስደተኛ?
ስዱድ የሚለውን ቃል ባህሩ ዘርጋው ግዛው በመዝገበ ቃላቱ ሲፈታው፣ በድፍኑ “ከአገሩ ወጥቶ የሄደ፤ ፈላሻ”>
ይለዋል።1 ለትምሕርት ወይም ለሥራ ወይም በፖለቲካ ምክንያት፤ ወ.ዘ.ተ. የወጣ ብሎ አይለየውም።
ባጭሩ፤ እንደኔ ማለት ነው። ከአገሬ ወጥቼ በባዕድ አገር መኖር የጀመርኩት በዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ሲሆን፣
እነሆ ሠላሳ ሰባተኛ ዓመቴ ላይ ነኝ።
ታዲያ አሁን ባለሁበት የመካከለኛ ዕድሜዬ፣ ሌትም ቀንም የምመኘው አገሬ ተመልሼ የምኖርበትን ዕድል
እንዲያፋጥንልኝ ነው። ከስደተኛ የኢትዮጵያ ልጆች እየደጋገምኩ የምሰማው ግን፤-
· “ለምን ብዬ ያለኝን የተመቸ ኑሮ ለማያስተማምን የኢትዮጵያ አስተዳደርና አስጊ ሕግ አጋልጠዋለሁ?”>
· “እንዴት ብዬ ሕግ በማይሠራበት አገርና ካልተማረ ሕዝብ መኻል እኖራለሁ?”
· “እዚህ ከብዙ ጥበቃና ድካም በኋል ያገኘሁትን ‘ነጻነት’፤ ብልጽግናና ዜግነት እንዴት ለማይስተማምን
የኢትዮጵያ ኑሮ እለውጠዋለሁ?”
እነዚህንና የመሳሰሉ እስትንፋሶችን ነው። እንዲሁም፤ ብዙዎች ‘ስደተኛ’>ወገኖቼ የራሳቸውንም ልምምድ ኾነ
የሰሙትን ሲይስተጋቡ፣ “እከሌ ቦሌ ሲ/ስትደርስ ተሰቃየ/ች፤ የባንክ ደብተር ለማስወጣት አስቸገረው/ራት፤
እከሌ/ሊትን አስፈራሩ/ሯት፤ ….ወ.ዘ.ተ. “>ይላሉ።
በከፊሉ የጊዜውን አስተዳዳሪዎችና የፖሊቲካ ፍልስፍናቸውን ከመጥላትማ የፈነጩ አስተያየቶች መሆናቸውን
አልዘነጋሁትም። አብዛኛዎቻችንም ለጉብኝትም ኾነ ለሥራ ስንሄድ የምንገነዘበው በወገናችን ላይ የተቃጣው
ችግር፤ ድህነት፤ በሽታ፤ ከዚህም አልፎ ተርፎ፣ በራሱ አስተዳዳሪዎች የሚሰነዘርበት ዕለታዊ ጭቆና
ያስመርረናል፤ ተስፋም ያስቆርጠናል። በስደት ኑሯችንም እያለን በየመገናኛ ብዙሀኑ የምንረዳው ይኼንኑ
የጊዜውን አስተዳዳሪዎችንና ፍልስፍናቸውን የበለጠ የሚያስጠላን እንጂ እምነታችን እንዲበረታ የሚያደርግ
አይደለም።
የዘንድሮውማ ‘በመብራት ኃይል እጥረት’>የቱን ያህል የከተማው ኗሪ እየደርሰበት ያለውን እንግልት እንዲሁም
ያሉት ፋብሪካዎች መዘጋታቸውን፣ የዝናብ እጥረት እንደተለመደው ስንት ሚሊዮን ወገናችንን ለረሃብ
እንደዳረገው፤ በብዙ ምክንያት የመጣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በአገር ውስጥ የቱን ያህል የዋጋ ግሽበትን
እንዳስከተለና ባሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ከእንዥብብ አልፎ ያረፈውን የኤኰኖሚ ነቀርሳ ያችን ድሀ አገሬን
ካቅሟ በላይ፤ መሸከም የማትችለውን ጭነት አስይዟታል።
በርግጥ አገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመርዳት በውጭ እየኖሩ መሥራት የሚሻልና
ቁልፍ የሆነ አስፈላጊ መፍትሄ መሆኑን የሚያምኑም የስደት ነዋሪዎችም ብዙ ናቸው። ይኼ እንዳለ ኾኖ እኔን
ያሳሳበኝ ግን
1. ሥልጣን ላይ ያይደለውንና ግራ በገባው ሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደጥፋተኛ፤
እንደባለምርጫ፤ እንደ አዳሚና የጊዜው አስተዳደር ተባባሪ ታይቶ ‘ገደል ይግባ’> የሚል ፍርድ
እየፈረድንበት ያለ ስለሚመስለኝ፤
2. በሁለቱም፣ ማለትም በገዢው አስተዳደር እና ለኢትዮጵያ ዕድገት፤ ብልጽግና፤ ልማት ‘አስፈላጊ’>
በሆነው ‘ስደተኛው’> ኢትዮጵያዊ መኻል አግባቢ ቋንቋ ባለመፈጠሩ፤
3. ‘ስደተኛው’> ኢትዮጵያዊ የውስጣዊውን ኢትዮጵያዊ መንፈስ ከአለበት ምቾት አብልጦ የቀሰቀሰው
ዘላቂ ወኔ ስላልተፈጠረ ነው።
የ‘ስደተኛው’> ኢትዮጵያዊን የማንነቱን ወኔ የመቀስቀስ ኃላፊነት የማን ይኾን? ባሁኑ ጊዜ ውጭ ነዋሪው
ኢትዮጵያዊ ይሰነዝራል ያልኳቸውን አስተሳሰቦችና ስሜቶች ማስተካከል የማን ሥራ ይኾን?
በቅርቡ አዲስ ሪፖርተር “ዝሆን አለመሆኔ እስኪጣራ ድረስስ!”2 በሚል አንቀጽ ከላይ ያነሳኋቸውንና የመሳሰሉ
ጥያቄዎችን ከተነተነ በኋላ …”መፍትሔው በመንግሥት እጅ፣ በኢሕአዴግ እጅ ነው” ብሎ ደምድሞታል።

እውነትም የጊዜው ሽከታ፤ በየቤንመረቡ አገር ነክ ድኅረ ገጽ የምናነበውም ኾነ ከዘመድ አዝማዶቻችን
የምንሰማው፣ በስደተኞች ወገኖቼ ልብ ውስጥ ያለውን ያለመተማመን ስሜት የሚያዳብር እንጂ እውነተኛውን
ልባዊ ወኔ የሚቀሰቅስ አይደለም።
የወቅቱ መንግሥት በአስተዳደር፤ በምጣኔ ሃብት፤ በፖሊቲካ፤ በፍትሕ ረገዶች የሚጫወተው ሚና እና ተግባር
ሁሌም በአገሪቱ ውስጥ ዘላቂ ሰላም እና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፡ ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ
እድገት እንዲፋጠን፤ የሕዝቡን የነጻ ፍላጎትና የሕግን የበላይነት የሚያረጋግጥ ተግባር መሆን አለበት። የአገሪቱ
ሕገ መንግሥትም እነኚሁኑ መለኪያዎች ነው በመግቢያው አንቀጽ ላይ ያሰፈረው።3
በነኚህ መለኪያዎች አኳያ አስፈላጊና ጥሩ የልማት ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ፤ እንዲሁም የሕዝብን
መተዳደሪያ ሕግ እንዳስፈላጊነቱ እያሻሻለ እንደሆነ፣ እውን አገሪቱን ወደ ትክክለኛ የስልጣኔ መንገድ እየመራ
ከሆነ፣ በሰፊው ለሕዝቡ ማቅረብና ማስተባበር፤ ማሳመን አለበት። የመንግሥት ወኪሎች (ከላይ እስከታች)
ሕዝብን ለማገልገል የተመረጡና የተሰማሩ መሆናቸውን ሙሉ በሙሉ እንደሚያምኑበት በተግባራቸውና
በሕዝብ ተጠያቂነታቸው ሰፊውን ሕዝብ ማሳመን አለባቸው። ከዚህ ጋር አብሮ የሚራመደው ስርዐት ደግሞ፤
እኒህ የመንግሥት ወኪሎች የሥልጣን ድርጊታቸው በተዛባ ጊዜ በሕዝብ ነጻ ድምጽ ከሥልጣን ሲወገዱ፤
ወንጀለኛ ከሆኑም በሕግ ተጠያቂነታቸው በይፋ ሲታይና ሲተገበር ነው።
እኛንም ከስልጣኔው መኻል የምንገኘውን የኢትዮጵያ ልጆች፤ ሥልጣን ላይ ያይደለውንና ግራ የገባውን
ሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከድህነት ቀንበር ለማላቀቅ፤ ለማስተማር፤ ለማበልጸግ፤ ለመምራት እንዲሁም
ከጭለማ ወደ ብርኃን ለማሸጋገር አስተዋጽኦዋችን የቱን ያህል እንደሚያስፈልግ ማስገንዘብና ማሳመን የማን
ኃላፊነት ነው? የወቅቱ መንግሥት ነዋ!!
ታዲያ የጊዜው ሥልጣናዊ ሸካቾች፣ ቢጮህ፤ ‘እሪ ያገር ያለህ፣ የወገን ያለህ’> ቢባል፤ ለኃያላን መንግሥታት
አቤቱታ ቢደረደር፤ የማይሰሙ ሲሆኑ፤ እኛ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ዝም ብለን የወገናችንን መርዶ በሩቁ
እንጠብቅ? ወይስ ‘አገሬ ተመልሼ የምኖርበትን፤ ወገኖቼን ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ቀንበር የማስለቅቅበትን፤
ሕገ መንግሥቱንና ያዘላቸውን የኢትዮጵያን ሰፊ ህልሞች እውን ለማድረግ ከወገኖቼ ጋር ለመሰለፍ ዕድል
ተግቼ ልፈልግ፣ ልከታተል’ ባዮች እንሁን?
ለአገራችንና ለወገናችን ዘላቂ መፍትሄና ትግበራ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን
ባለቤትነታቸውን ማስረገጥና ማረጋገጥ ኃላፊዎቹ መቼም ቢሆን እኛው ኢትዮጵያውያን (ስደተኞቹን አጠቃሎ)
ስለሆንን የኢትዮጵያዊነት ወኔያችንን እራሳችን እንቀስቅስ። ስደተኛው ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ዕጣ
የተሳሰረ፣ የማይካድ፣ ልባችን የሚያምንበት፣ እንቅልፍ የሚያሳጣንና የዘላለም ቅስቀሳችን መሆኑን እንቀበል።
ከ ሰይፈ ገብርኤል ኪዳኔ
ለንደን
ታሕሣሥ ፭ ቀን »¼½ ዓ.ም.
1 “ዘርጋው የአማርኛ መዝገበ ቃላት”>ከባህሩ ዘርጋው ግዛው፤ ¾ ¿¼ÀÁ ዓ.ም
2 አዲስ ረፖርተር፣ ዕሮብ ሰኔ »Á ቀን »¼½ ዓ.ም
3 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት

Please Select Embedded Mode To Show The Comment System.*

Postagem Anterior Próxima Postagem